Ethiopian Radation Protection Authority Ethiopian Radation Protection Authority

የጨረራ ውስድ መጠን ለማስለካት የጨረራ ውስድ መጠን ለማስለካት

የድርጅቱ ስም፡ ዶዚሜድ የላብራቶሪ ፍተሻ

(የጨረራ ውስድ መጠን መለኪያ)

ስልክ ቁጥር፡- 0116900239/011878154

ሞባይል፡- 0961279384/85

ኢ-ሜይል፡- dosimedaddis@gmail.com

የቢሮ አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ ጎላጎል ሕንፃ

              11ኛ ፎቅ

              ቢ.ቁ 1103

 

Organization: Dosi med Laboratory test

Address: 0116900239/011878154

Mobile: 0961279384/85

Email: dosimedaddis@gmail.com

Office: 22 Mazoriya Golagol 

             Building 11th Floor

            Office No. 1103  

ERPA's Proclamation ERPA's Proclamation

Ethiopian Radiation Protection Authority Proclamation No 1025/2017

Click here to download ERPA's Proclamation NO. 1025/2017

 

Ethiopian Radiation Protection Authority Page Ethiopian Radiation Protection Authority Page

Inspection

Conducting Inspection based on: Regular inspection Programme and, Request from the customer,Verification Inspection, Inspection based on past profile of the institution.

Enforcement

Possible actions for non-compliance: Formal instructions assured and correct the infraction, Written warning for non – compliance, Suspension of or restrictions on, operation until regulatory infraction or safety condition is corrected.

Organizational structure of ERPA

The solid organazational structural unit of ERPA. ERPA is a Federal Government body that control and regulate the import,export, use, transport, dispose of, etc any source of radiation.

ERPA Photo Display ERPA Photo Display

lll
IRRS Mission In Ethiopia 2017
Metting
Discussion
Actual Evaluation at Tse Tse Fly
Women's Day celebration
MOU Signing with Haromaya University
MOU Signing with Diredawa University
MOU Signing with SUDAN
MOU Signing with SUDAN
Discussion with the US. Nuclear Regulatory Commission, in Ethiopia Addis Ababa
MOU Signing with USNRC
IAEA 63rd General Conference at Vienna, Austria

Asset Publisher Asset Publisher

ልዕለ ሀምራዊ ጨረራ ጉዳቱና መከላከያው

ልዕለ ሀምራዊ ጨረራ ጉዳቱና መከላከያው (በታደለ ነጋሽ)

አዮን ፈጣሪ ካልሆኑት የጨረራ አይነት ምድብ ውስጥ የሚገኘውና ልእለ ሀምራዊ ጨረራ (Ultra Violate Radiation (UVR)) በመባል ለሚታወቀው ጨረራ ከመጠን በላይ ሰውነታችን ቢጋለጥ በአይንና ቆዳ ላይ ከቀላል አንስቶ እስከ ከፍተኛ ጉዳት ማለትም የአይንን እይታ እስከመከለል እና በቆዳ ላይ ካንሰር እስከማስከተል ድረስ ችሎታ አለው፡፡

ለመሆኑ በልዕለ ሀምራዊ ጨረራ እንዴት ልንጋለጥ እንችላለን?

ልዕለ ሀምራዊ ጨረራ በተፈጥሮ ከፀሀይ ብርሃን ጋር ተያይዞ የሚመጣ እንዲሁም ከተለያዩ ሰው ሰራሽ ልዕለ ሀምራዊ ጨረራ አመንጪዎች (uv lamps, Black Lamps, በሀገራችን እምብዛም በማይታወቀው የልዕለ ሀምራዊ ጨረራ መሞቂያ/መጋለጫ አልጋ (UV Tanning Bed)፣UV Tanning Beds, Welding Arcs, etc) የሚመነጭ እንደመሆኑ በተለያየ ሁኔታ ለጨረራው ልንጋለጥ እንችላለን፡፡

የሰው ልጅም ልዕለ ሀምራዊ ጨረራን ለተለያዩ አገልግሎቶች ይጠቀምባቸዋል፡፡ ለአብነትም  ወላጆች ህጻናት ልጆቻቸውን ፀሀይ የሚያሞቁበት ምክኒያት ቫይታሚን ዲ እንዲያገኙ በማሰብ ሲሆን ለቫይታሚኑ መመረት ዋነኛው ምክንያት ደግሞ ልዕለ ሀምራዊ ጨረራ ነው፡፡ የአለም ጤና ድርጅትም የሰው ልጅ በየቀኑ ከ5 እስከ 15 ደቂቃ ፀሀይ  ለ2 እና 3 ቀናት ያህል በሳምንት ቢያገኝ በቂ ቫይታሚን ዲ ሊኖረው እንደሚችል ጠቁሟል፡፡

ከሰው ሰራሽ አመንጪዎች የሚመነጩ ልዕለ ሀምራዊ ጨረራን የተለያዩ ተህዋስያንን በመግደል ለማምከኛነት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ በምሳሌነትም የህክምና መሳሪያዎችን አገልግሎት ከሰጡ በኋላ ተሃዋስያንን በዚሁ ጨረራ እንዲሞቱ ይደረጋል፤ ውሀን ከጀርምና ከመሳሰሉት እንዲጸዳ ይደረግበታል፤የጸጉር ቤት መሳሪያዎችን ለማጽዳት፣ ለነፍሳት መግደያ የመሳሰሉ አገልግሎቶች ላይ ይውላል፡፡

አንድ ሰው ለልዕለ ሀምራዊ ጨረራ ከመጠን በላይ የሚጋለጥ ከሆነ በአይኑ ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከማሳከክ ጀምሮ ዕይታን እስከ መጋረድ የሚያደርስ ሲሆን በቆዳውም ላይ ከመለብለብ እስከ ቆዳ ካንሰር ደረጃ ሊያደርስ ወይም ሊያስከትልበት ይችላል፡፡ አብዛኛው የቆዳ ካንሰርም ከዚሁ የልዕለ ሀምራዊ ጨረራ መጋለጥ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ነው፡፡

በመሆኑም ልዕለ ሀምራዊ ጨረራ ሊያስከትል ከሚችለው ጉዳት ለመከላከል የተለያዩ ዘዴዎችን መከተል ወይም ተግባራዊ ማድረግ ግድ ይላል፡፡

ከፀሀይ ጋር ተያይዞ በፀሀያማ እለት በአማካይ ከቀኑ 4፡00 እስከ 8፡30 ድረስ ባለው ሰዓት ውስጥ ተገቢ የሆኑ አልባሳት እንደ ኮፍያ፣ ጃንጥላ፣ መነጽር፣ የመሳሰሉት ቢደረጉ እንዲሁም ከሰው ሰራሽ ልዕለ ሀምራዊ ጨረራ ስራ ጋር ተያይዞ ለዚሁ የጨረራ አይነት መከላከያነት የሚውሉ ተገቢው አልባሳት እንደ ሄልሜት፣ መነጽር፣ የቆዳ ጓንት፣ ረዢም እጅጌ ያላቸው አላባሳት፣ የቆዳ ሽርጦች (Helmets, Goggles, Leather gloves, Long-sleeve jackets, etc) የመሳሰሉትን በመልበስ መከላከል ይቻላል፡፡

በብየዳ ወቅት የብየዳ ሰራተኛው ተገቢውን አልባሳት በመልበስ ስራውን ሊያከናውን የሚገባ ሲሆን ሌሎች ባቅራቢያው የሚገኙ ሰዎች ግን ከብየዳ ስራው በሚወጣ ጨረራ እንዳይጋለጡ ከለላ ሊጠቀም ይገባል፡፡

Average (0 Votes)


No comments yet. Be the first.