Ethiopian Radation Protection Authority Ethiopian Radation Protection Authority

የጨረራ ውስድ መጠን ለማስለካት የጨረራ ውስድ መጠን ለማስለካት

የድርጅቱ ስም፡ ዶዚሜድ የላብራቶሪ ፍተሻ

(የጨረራ ውስድ መጠን መለኪያ)

ስልክ ቁጥር፡- 0116900239/011878154

ሞባይል፡- 0961279384/85

ኢ-ሜይል፡- dosimedaddis@gmail.com

የቢሮ አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ ጎላጎል ሕንፃ

              11ኛ ፎቅ

              ቢ.ቁ 1103

 

Organization: Dosi med Laboratory test

Address: 0116900239/011878154

Mobile: 0961279384/85

Email: dosimedaddis@gmail.com

Office: 22 Mazoriya Golagol 

             Building 11th Floor

            Office No. 1103  

ERPA's Proclamation ERPA's Proclamation

Ethiopian Radiation Protection Authority Proclamation No 1025/2017

Click here to download ERPA's Proclamation NO. 1025/2017

 

Ethiopian Radiation Protection Authority Page Ethiopian Radiation Protection Authority Page

Inspection

Conducting Inspection based on: Regular inspection Programme and, Request from the customer,Verification Inspection, Inspection based on past profile of the institution.

Enforcement

Possible actions for non-compliance: Formal instructions assured and correct the infraction, Written warning for non – compliance, Suspension of or restrictions on, operation until regulatory infraction or safety condition is corrected.

Organizational structure of ERPA

The solid organazational structural unit of ERPA. ERPA is a Federal Government body that control and regulate the import,export, use, transport, dispose of, etc any source of radiation.

ERPA Photo Display ERPA Photo Display

lll
IRRS Mission In Ethiopia 2017
Metting
Discussion
Actual Evaluation at Tse Tse Fly
Women's Day celebration
MOU Signing with Haromaya University
MOU Signing with Diredawa University
MOU Signing with SUDAN
MOU Signing with SUDAN
Discussion with the US. Nuclear Regulatory Commission, in Ethiopia Addis Ababa
MOU Signing with USNRC
IAEA 63rd General Conference at Vienna, Austria

Asset Publisher Asset Publisher

ቀጠ-መስመራዊ አስሸምጣጭ የሕክምና መሳሪያ(Medical Linear Accelerator, LINAC)

ቀጠ-መስመራዊ አስሽምጣጭ ከፍተኛ ጉልበት ያላቸውን X-ራጆች ወይም ኤሌክትሮኖችን ከእብጠቱ ቅርፅ ለማስማማት የሚረዳና ጤናማ ኅብረ-ሕዋሳትን የከበበውን የነቀርሳ(cancer) ሕዋስ ለመግደል የሚጠቅም መሳሪያ ነው፡፡

በሐኪሙ ከታዘዘው የጨረራ መጠን የበለጠ መጠን እንዳያስወጣ ለመቆጣጠር የሚረዱ አብረው የተሰሩ የጨረራ ደኅንነት መከላከያ ዘዴዎች ያሉት ሲሆን መሳሪያው በትክክል መስራቱን  የሕክምና ፊዚካ ምሁር (medical physicist) በየጊዜው ይከታተለዋል፡፡ በቀጠ-መስመራዊ አስሸምጣጭ የሕክምና መሳሪያ የጨረራ ሕክምና ለማካኼድ ከተወሰነ የታካሚው የጨረራ የነቀርሳ ሕክምና ልሂቅ (radiation oncologist) ከጨረራ ሥነ-ውስድ ልሂቁ (radiation dosimetrist) እና ከሕክምና ፊዚካ ምሁሩ (medical physicist) ጋር በመመካከር የሕክምና መርሃ-ግብሩን ማውጣት ይጠበቅበታል፡፡ የታካሚው ሐኪም ሕክምናው ከመጀመሩ በፊት የሕክምና ኺደቱን የጊዜ መረሃ-ግብር እንደገና ማየት(ማረጋገጥ) እና እያንዳንዱ ሕክምና በትክክል በተወሰነው ሁነት መካኼዱን መከታተያ የሚሆን የጥራት ማረጋገጫ መራኄ-ድርጊት(procedures) ማዘጋጀት አለበት፡፡

                                     

ቀጠ-መስመራዊ አስሸምጣጭ የሕክምና መሳሪያ አገልግሎት

ቀጠ-መስመራዊ አስሸምጣጭ የሕክምና መሳሪያ በዋናነት በአፍአዊ አመልማሎ የጨረራ ሕክምና (external beam radiation therapy) ነቀርሳን ለማከም የሚውል መሳሪያ ሲሆን ሁሉንም ክፍላተ-አካል (organs) ለማከም ይጠቅማል፡፡ በአገልግሎት ወቅት ከፍተኛ ጉልበት ያላቸው የ X-ራጆችን ወይም ኤሌክትሮኖችን ወደ ታካሚው የነቀርሳ ሕዋስ ከባቢ ይልካል፡፡ ይህ የሕክምና ዘዴ  X-ራጆች ወይም ኤሌክትሮኖች ጤናማ ኅብረ-ሕዋሱን የከበቡ የነቀርሳ ሕዋሳትን እንዲገሉ ወይም እንዲያጠፉ ተደርጎ ይዘጋጃል፡፡ ቀጠ-መስመራዊ አስሸምጣጭ የሕክምና መሳሪያ ልማዳዊ ስልቶችን፣ ድምቀተ ልውጥ ጨረራ ሕክምናን (Intensity Modulated Radiation Therapy,IMRT)፣ ይዘተ ልውጥ ፈተት ሕክምናን (Volumetric Modulated Arc Therapy, VMAT)፣ ምስል መር ጨረራ ሕክምናን (Image Guide Radiation Therapy, IGRT)፣ ስልተቀረፃ ጨረራ ቀዶ-ሕክምናን (Stereotactic Radio-Surgery, SRS) እና ስልተ መቅረፀ -አካል ጨረራ ህክምናን (Stereotactic body Radiation Therapy, SBRT) በመጠቀም ሁሉንም ክፍላተ-አካላት ለማከም ያገለግላል፡፡

የቀጠ-መስመራዊ አስሸምጣጭ የሕክምና መሳሪያ የአሰራር መርኅ

ቀጠ-መስመራዊ አስሸምጣጭ የሕክምና መሳሪያ እንደራዳር ሁሉ ኤሌክትሮኖችን ሞገድ መር (wave guide) ተብሎ በሚጠራው የመሳሪያው ክፍል ለማስሸምጠጥ ሚሊዮንኛ ደቂቅ ሞገድን (micro wave) በመጠቀም ኤሌክትሮኖች ከከባድ ዒላማ ብረት አስተኔ ጋር ተጋጭተው ከፍተኛ ጉልበት ያላቸው  የX-ራጆች እንዲፈጥሩ ያደርጋቸዋል፡፡ እነዚህ ከፍተኛ ጉልበት ያላቸው የ X-ራጆችም ከመሳሪያው ሲወጡ ከታካሚው እብጠት ቅርፅ ጋር እንዲስማሙ ይደረጉና የጨረራ አመልማሎው የነቀርሳ ሕዋሱ ዘንድ  እንዲደርስ ይደረጋል፡፡ የጨረራ አመልማሎው የሚፈለገውን ቅርፅ እንዲይዝ የሚደረገው የማሽኑ ጫፍ ላይ ለዚህ ዓላማ በሚቀመጥ ባለብዙ ቅጠል አኮልኳይ (multileaf collimater) ነው፡፡ በሕክምናው ጊዜ ታካሚው ወደ ሁሉም አቅጣጫ መንቀሳቀስ በሚችል አልጋ ላይ ይተኛና በጨረር አመንጪ መሳሪያ ብርሃን (laser light) ትክክለኛ ቦታው ላይ ማረፉ ከተረጋገጠ በኋላ የጨረራ አመልማሎው በታካሚው ዙሪያ ከሚሽከረከር መቃን (Gantry) ተብሎ ከሚጠራው የመሳሪያው ክፍል ይወጣል፡፡ ይህ ጨረራ ለእብጠቱ ከየትኛውም ዜዌ (angle) የሕክምና አልጋውን በማንቀሳቀስና መቃን በማሽከርከር ይሰጣል፡፡

የቀጠ-መስመራዊ አስሸምጣጭ የሕክምና መሳሪያ ተቆጣጣሪ(ባለሙያ)

የሕክምና ቦታ ይዘቱንና የጨረራ ውስድ መጠኑን የታካሚው የነቀርሳ ሕክምና ልሂቅ (oncologist) ይወስነዋል፡፡ ይህን የተወሰነውን መጠን እንዴት ለታካሚው እንደሚሰጠው መወሰን እና መሳሪያው ያንን መጠን ለመስጠት የሚወስደውን ጊዜ ማስላት ደግሞ የሕክምና ፊዚካ ምሁሩና (medical physicist) የጨረራ የሥነ-ውስድ መጠን ልሂቁ (dosimetrist) ድርሻ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የጨረራ ሐኪሙ (radiation therapist) የቀጠ-መስመራዊ አስሸምጣጭ መሳሪያውን ተጠቅሞ ለታካሚው የቀን ከቀን የጨረራ ሕክምናውን ያካኼድለታል፡፡

በሕክምናው ወቅት የሚደረግ የደኅንነት አጠባበቅ

የታካሚውን፣ የጨረራ ሕክምና ሰራተኞችንና የማኅበረሰቡን ደኅንነት ለማረጋገጥ  የሚከተሉት ተግባራት በትክክል መከናወን አለባቸው፡፡

  • ሕክምናው ከመካኼዱ በፊት መራኄ-ድርጊት በማውጣትና ደጋግሞ በማየት እንዲሁም የጥራት ማረጋገጫ መራኄ-ድርጊቶችን በማካኼድ ሕክምናው በዕቅዱ መሠረት እንዲከናወን ማስቻል፡፡
  • የነቀርሳ ሕክምና ልሂቁ ከወሰነው የጨረራ መጠን በላይ እንዳያወጣ መሳሪያውን መከታተል፡- ሁልጊዜ  ታካሚዎቹ ወደ ሕክምና ከመግባታቸው በፊት የጨረራ ሐኪሙ መሳሪያው በትክክል መስራቱንና ድምቀተ ጨረራ አመልማሎው (radiation intensity in the beam ) ዓይነተ-አንድ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሕክምና ፊዚካ ምሁሩ ጥልቅ ወርኃዊና ዓመታዊ የመሳሪያ ፍተሻ ማድረግ አለበት፡፡ ዘመናዊ አስሸምጣጭ መሳሪያዎች ሁሉም የተቀመጡት መሥፈርቶች እስካልተሟሉ ድረስ መሳሪያው እንዳይነሳ (turnoff) የሚያደርግ ውስጣዊ መቆጣጠሪያ አላቸው፡፡ በሕክምናው ወቅትም የጨረራ ሐኪሙ ዝግ የኤሌክዙር መጽሔተ ምስል መከታተያ (closed circuit television monitor) በመጠቀም ታካሚውን ሳያቋርጥ መከታተል አለበት፡፡ በሕክምናው ጊዜ አስፈላጊ ሲሆን ታካሚው ለጨረራ ሐኪሙ እንዲናገር የሚረዳ የድምፅ ማስተላለፊያ መሳሪያም (micro phone) በሕክምና ክፍሉ ውስጥ ይቀመጣል፡፡ የአመልማሎ ቦታው ከመጀመሪያ ዕቅዱ አለመለየቱን ለማረጋገጥ ወደበ-ፊልሞች (port films) ወይም እንደ ቅምብብ አመልማሎ ሲቲ መቃኛ (cone beam CT scan)  ያሉ ሌሎች የምስል መሳሪያዎች በመደበኛነት መታየት አለባቸው፡፡ የቀጠ-መስመራዊ አስሽምጣጭ መሳሪያ የጨረራ ሐኪሞችን፣ ሰራተኞችንና ከውጪ ያለን ማናኛውንም ሰው  ከፍተኛ ጉልበት ካላቸው  X-ጨረራዎች ለመከላከል    ቀጠ-መስመራዊ አስሸምጣጭ መሳሪያዎች የእርሳስ (lead) እና እንደሚያመነጩት የጉልበት መጠን በከፍተኛ ጥንቃቄ የተዋቀሩ ወፍራም የአርማታ (concrete) ግድግዳዎች ባሉት ክፍል ውስጥ ይቀመጣል፡፡ የጨረራ ሐኪሙ የቀጠ-መስመራዊ መሳሪያውን ማስነሳት (turn on) ማድረግ ያለበት ከሕክምና ክፍሉ ውጪ ሆኖ ነው፡፡  

ምንጭ፡-

 

Average (0 Votes)


No comments yet. Be the first.