Ethiopian Radation Protection Authority Ethiopian Radation Protection Authority

የጨረራ ውስድ መጠን ለማስለካት የጨረራ ውስድ መጠን ለማስለካት

የድርጅቱ ስም፡ ዶዚሜድ የላብራቶሪ ፍተሻ

(የጨረራ ውስድ መጠን መለኪያ)

ስልክ ቁጥር፡- 0116900239/011878154

ሞባይል፡- 0961279384/85

ኢ-ሜይል፡- dosimedaddis@gmail.com

የቢሮ አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ ጎላጎል ሕንፃ

              11ኛ ፎቅ

              ቢ.ቁ 1103

 

Organization: Dosi med Laboratory test

Address: 0116900239/011878154

Mobile: 0961279384/85

Email: dosimedaddis@gmail.com

Office: 22 Mazoriya Golagol 

             Building 11th Floor

            Office No. 1103  

ERPA's Proclamation ERPA's Proclamation

Ethiopian Radiation Protection Authority Proclamation No 1025/2017

Click here to download ERPA's Proclamation NO. 1025/2017

 

Ethiopian Radiation Protection Authority Page Ethiopian Radiation Protection Authority Page

Inspection

Conducting Inspection based on: Regular inspection Programme and, Request from the customer,Verification Inspection, Inspection based on past profile of the institution.

Enforcement

Possible actions for non-compliance: Formal instructions assured and correct the infraction, Written warning for non – compliance, Suspension of or restrictions on, operation until regulatory infraction or safety condition is corrected.

Organizational structure of ERPA

The solid organazational structural unit of ERPA. ERPA is a Federal Government body that control and regulate the import,export, use, transport, dispose of, etc any source of radiation.

ERPA Photo Display ERPA Photo Display

lll
IRRS Mission In Ethiopia 2017
Metting
Discussion
Actual Evaluation at Tse Tse Fly
Women's Day celebration
MOU Signing with Haromaya University
MOU Signing with Diredawa University
MOU Signing with SUDAN
MOU Signing with SUDAN
Discussion with the US. Nuclear Regulatory Commission, in Ethiopia Addis Ababa
MOU Signing with USNRC
IAEA 63rd General Conference at Vienna, Austria

Asset Publisher Asset Publisher

የጨረራ ሕክምና (RADIATION THERAPY OR RADIOTHERAPY)

የጨረራ ሕክምና ምንነት

የጨረራ ሕክምና በዋናነት ነቀርሳን(cancer) ለማከም የሚያገለግል ሲሆን የደም ዝውውር መዛባት አልፎ አልፎም የታይሮይድ ዕጢ በሽታን /thyroid disease/፣ የደም ብክለትን(blood disorder)  እና  ከነቀርሳ ነጻ የሆኑ እድገቶችን(non-cancerous growth) ለማከም ይጠቅማል፡፡ በተወሰነ ቦታ ላይ የተወሰነ  እብጠትን (tumors) ያማከለ የጨረራ መጋለጥን በመጠቀም ይካኼዳል፡፡ ጨረራ  እብጠትን  የማስታገስ ወይም ከፊል ፈውስን ያመጣል፡፡ ምንም እንኳ የጨረራ ሕክምና አደገኛ ያልሆኑ(non-malignant) ፣ እንደ ገር እብጠትን (benign tumors) እና  የሰውነት  መጉረብረብ፡ መመረዝ (inflammatory conditions) ጭምር ለማከም ቢጠቅምም በዚህ ጽሑፍ የምናየው ግን የነቀርሳ ሕክምናን ለማካኼድ ያለውን ጥቅሙን  ነው፡፡ የጨረራ ሕክምና የነቀርሳ ሕዋስን ዘረመል(D.N.A) በመስበር እድገቱን ለመግታትና ለመከፋፈል፣ ለመግደል፣የእድገት ፍጥነቱን ለመቀነስና  የቀዶ-ሕክምና ለማካኼድ እንዲያመች ዕጢን (እብጠትን ) ለማጨማተር ከፍተኛ የሞገድ ኃይልን ይጠቀማል፡፡ የጨረራ ሕክምና አንዳንዴ ብቻውን አንዳንዴም የነቀርሳ ሕክምና ልሂቁ(radiation therapy specialist) ከወሰነ እንደኬሚካዊ/ኬሚፈውስ/ ሕክምና (chemotherapy treatment) ካሉ ዘዴዎች ጋር በማቀናጀት ሊሰጥ ይችላል፡፡

የጨረራ ሕክምና ዓይነቶች(types of radiation therapy)

ሁለትየጨረራ ሕክምና ዓይነቶች አሉ፡፡ እነሱም፡-

 1. አፍአዊ-አመልማሎ(external beam) የጨረራ ሕክምና፡- ይህ ዓይነቱ ሕክምና የጨረራ አመልማሎ(beam) ከውጪ ከተቀመጠ መሳሪያ የሚታከመውን የአካል ክፍል ዒላማ አድርጎ በነቀርሳ የተጠቃው ሕዋስ ለጨረራው እንዲጋለጥ የሚደረግበት የሕክምና ዓይነት ነው፡፡

        

 1. ውሳጣዊ-የጨረራ ሕክምና(internal radiation therapy)፡- ይህ ደግሞ ራዲዮአክቲቭ ቁስ አካል በነቀርሳ ኅብረ-ሕዋሱ ውስጥ ወይም ከነቀርሳ ኅብረ-ሕዋሱ ጥግ በጊዜያዊ አሊያም በቋሚነት በማስቀመጥ የነቀርሳ ሕዋሱ የሚታከምበት የሕክምና ዓይነት ነው፡፡

የጨረራ ሕክምና ጥቅሞች

የጨረራ ሕክምና በግልፅ የተለየን ነቀርሳ ለማከም በሐኪም ምክረ-ሀሳብ ብቻ የሚፈቀድ ሕክምና ነው፡፡ በውስን አካል ላይ ያረፈና በግልፅ የተለየ ነቀርሳ ሙሉ የነቀርሳ ኅብረ-ሕዋሱን ዒላማ አድርጎ ለጨረራ ለማጋለጥ ስለሚረዳ ለጨረራ ሕክምና ምቹ ይሆናል፡፡ በተቃራኒው እንደ ደም ነቀርሳ ያሉ አንዳንድ ነቀርሳዎች ደግሞ የሚታከሙት ሙሉ አካልን ለጨረራበማጋለጥ ስለሆነ ለጨረራ ሕክምና ምቹ አይደሉም፡፡

ነቀርሳን ለማከም የጨረራ ሕክምና፡-

ሀ. ብቻውን፡- የሽንት ፊኛ መግቢያ ላይ የሚገኝ ቱቦ ነቀርሳን(prostate cancer) እና የማንቁርት እብጠትን(tumor of the larynx) ለማከም

ለ. ከቀዶ-ሕክምና ጋር፡- የጨረራ ሕክምና ከነቀርሳ ቀዶ ሕክምና በፊት ወይም በነቀርሳ ቀዶ-ሕክምና ጊዜ እብጠትን ለማኮማተር፤ ከቀዶ- ሕክምና በኋላ ቀሪ የነቀርሳ ሕዋሳትን ሕማም ለመቀነስ ስራ ላይ ሊውል ይችላል፡፡

ሐ. ከኬሚካዊ ሕክምና (chemotherapy)፡- ጋር ሊታዘዝ ይችላል፡፡

የጡት፣ የጨጓራ፣ የጉሮሮ(የምግብ ቧንቧ)እና የትልቅ አንጀት(rectum) የነቀርሳ ሕዋሳት ሦስቱንም መንገዶች በመጠቀም ሊታከሙ ይችላሉ፡

የጨረራ የማስታገሻ ሕክምና(palliative radiotherapy)

የጨረራ ሕክምና ነቀርሳን ለማከም ከማገልገሉ በተጨማሪ ሙሉ በሙሉ ያልተፈወሱ እና በሰፊው የተዛመቱ የነቀርሳ ሕዋሳትን የሕማም ስሜቶች ለማስታገስ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሕክምና የጨረራ የማስታገሻ ሕክምና በመባል የሚታወቅ ሲሆን የእብጠቱን መጠንና ሕማም ለመቀነስ ይጠቅማል፡፡ ሌላው ከአንጀት፣ ከጡት ወይምከሽንት ፊኛ የመግቢያ ቱቦ የነቀርሳ ሕዋሳት ወደ አጥንትና ሌሎች ክፍሎች የተዛመተን የነቀርሳ ሕዋስ በማከም የበሽተኛውን ሕይወት ለማራዘም ይጠቅማል፡፡ በጨረራ ሕክምና የማይድን የነቀርሳ ሕዋስ ከፍተኛ ስቃይ ያላቸው የአጥንት ነቀርሳዎች እንዳይፈጠሩ ለማድረግ (ተዛምቷቸውን በማስቆም) እና ደካማ አጥንቶችን በማጠንከር ሕማምን ለመቀነስ ያገለግላል፡፡

የጨረራ የማስታገሻ ሕክምናዎች የሚከተሉትን አገልግሎቶች ለመስጠትም ይውላሉ፡-

 • የእብጠት መጠንን በመቀነስ ግፊትን ማስታገስ
 • እንደራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽና የራስ ማዞር የመሳሰሉ የአእምሮ ካንሰር ምልክቶችን ማከም
 • እንደ ደረት ሕማምና የትንፋሽ ማጠር ያሉ የጨጓራ ነቀርሳ ምልክቶችን ማከም
 • መድማትን፣ ማመርቀዝንና  ተዛማጅ እብጠትን(ulcerating tumor) መቆጣጠር ወይም ማከም
 • ኃይለኛ ዓቢይ ደም መላሽ መሰናክልት(superior vena cava obstruction, SVCO) በመባል የሚታወቀውን የራስና የአንገት የነቀርሳ ሕዋሳት ደምን ወደ ልብ እንዳይመለስ የሚያደርጉትን እገዳ በማጨማተር ማከም

የጨረራ ሕክምና የጎንዮሽ ጉዳቶች(side effects of radiotherapy)

የጨረራ ሕክምና የጎንዮሽ ጉዳቶች የሚከሰቱት በነቀርሳ ያልተጠቁ ሕዋሳት በሕክምና ወቅት ለጨረራ ሲጋለጡ ነው፡፡ የጨረራ ሕክምና ለነቀርሳ ሕዋሳትም ይሁን በነቀርሳ ላልተጠቁ ሕዋሳት የሞገድ ኃይሉን  የሚያሳርፈው (የሚተረጉመው) በተመሳሳይ መንገድ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የነቀርሳ ሕዋሳት ራሳቸውን በፍጥነት የማራባት ፍላጎት ስላላቸውና ለማገገም የሚወስዱት ጊዜ በጣም ረዥም ስለሆነ ለሕክምና ውጤቱ የበለጠ ተጋላጭ ናቸው፡፡  የጨረራ ሕክምና የጎንዮሽ ጉዳቶች በሚታከመው ሰው፣በሚታከመው የአካል ክፍል፣ በታካሚው አጠቃላይ የጤና ሁነት እና በጨረራው ዓይነትና የውስድ መጠን መሠረት የአጭር ጊዜ ጉዳትና የረዥም ጊዜ ጉዳት በመባል በሁለት ይከፈላሉ፡፡

 

 የጨረራ ሕክምና የአጭር ጊዜ የጎንዮሽ ጉዳቶች(short-term side effects of radiotherapy)

የአጭር ጊዜ የጨረራ ሕክምና የጎንዮሽ ጉዳቶች የሚባሉት፡-

 • ድካም (fatigue or lethargy)
 • የቆዳ መቆጥቆጥ/ቡጉንጅ፣እዥ መቋጠር፣መላላጥ ወዘተ(skin irritation)
 • ከመድኃኒቱ (ከሕክምና ኺደቱ) ጋር ተያያዥ የሆኑ ጉዳቶች(effects specific to the area  of treatment) ለምሳሌ የፀጉር መርገፍ፡ የሽንት ፍሰት ችግር፡ ማቅለሽለሽ፡ ትውኪያ፡ ተቅማጥ ወዘተ)
 • የኅብረ-ሕዋሳት  መቆጣት(tissue inflammation) ለምሳሌ የጉሮሮ (ምግብ ቧንቧ) ሕማም(esophagitis) ፣የሳምባ ምች(pneumonitis)፣ የጉበት ብግነት(hepatitis)
 • አልፎ አልፎ የነጭ የደም ሕዋሳት እና ደም እንዲረጋ የሚያደርጉ ሕዋሳት ቁጥር መቀነስ ወ.ዘ.ተ ናቸው

የጨረራ ሕክምና የረዥም ጊዜ የጎንዮሽ ጉዳቶች (long-term side effects of radiotherapy)

የረዥም ጊዜ የጎንዮሽ ጉዳቶችም ሕክምናው በሚካኼድበት የአካል ክፍል የሚወሰኑ ሲሆን የሚከተሉትን ያካትታል፡-

 • የአካል መገተርና ውስን እንቅስቃሴ ማካኼድ
 • በደም ቧንቧዎች መስፋት ምክንያት የሚመጣ የቆዳ መቅላትና ለረዥም ጊዜ የማይድን ቁስል
 • በጨረራ ሕክምና ወቅት በሚከሰት የአንጀት መጎዳት ምክንያት የሚመጣ ተቅማጥና መድማት
 • የእድገንጥር(hormone) ችግር(ወረደ -ፔት ዕጢ/hypopitutarism/፣ወረደ-ታይሮድ ዕጢ/hypothyroidism/፣ የአፍ ድርቀት፣ የማስታወስ ችሎታን ማጣትና ምክነት)
 • በጨረራ መጋለጥ የሚመጣ ውልዴ-ነቀርሳ (second cancer)፡- አልፎ አልፎ ቢሆንም የለስላሳ ኅብረ-ሕዋሳት በነቀርሳ መጠቃት (soft tissue sarcoma) በከፍተኛ የጨረራ መጠን ምክንያት ሊመጡ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን የታከመ ነቀርሳ እንደገና የመከሰት ስጋት በጨረራ መጋለጥ ምክንያት ሊመጣ ከሚችለው አዲስ(ውልዴ) የነቀርሳ ስጋት የበለጠ ነው፡፡

ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉም ምሳሌዎች ግን ከሁሉም ዓይነት የጨረራ ሕክምና አይመነጩም፡፡ የረዥም ጊዜ የጎንዮሽ ጉዳት የመከሰት ዕድል የሚወሰነው በዋናነት በታካሚው ግለሰብ ነው፡፡ ስለዚህ የጨረራ ሕክምናን የመረጠ ሰው ሕክምናውን ከሚከታተለው የሕክምና ቡድን የጉዳት ስጋቱንና ጥቅሙን ምጥነት (balance b/n risks and benefits) በተመለከተ ምክር ማግኘት አለበት፡፡

 

ምንጭ፡  

 • MacGill, Markus. "What to know about radiation therapy?" Medical News Today. MediLexicon, Intl., 16 Feb. 2018. Web.
 • 14 Nov. 2018. <https://www.medicalnewstoday.com/articles/158513.php

 

 

 

Average (0 Votes)


No comments yet. Be the first.