መግለጫ

በዚህ ዳይሬክተሪ ስር የገቡ ቴክኖሎጂዎች በተቋሙ 2007 ዓ.ም ሀገር በቀል ቴክኖሎጂ የዳሰሳ ጥናት ወቅት የተሰበሰቡ ናቸው፡፡ የተሰበሰቡትም ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ከቴ/ሙያ ት/ማ/ተቋማት እና ከግለሰብ የፈጠራ ባለሙያዎች ነው፡፡ ቴክኖሎጂዎቹም ቀድሞ የነበሩ ቴክኖሎጂዎች መሰረት በማድረግ ማሻሻያ የተደረገባቸውና ከውጪ እንዲሁም ሀገር ውሰጥ ከነበሩት የተቀዱ ናቸው፡፡ ዳይሬክተሪው በአጠቃላይ ቴክኖሎጂዎቹ የሚገኙበት አድራሻ፣ ስለ ቴክኖሎጂው አጠቃላይ መረጀና የቴክኖሎጂው ዘርፍ እንዲሁም ፎቶ ይዞል፡፡ የቴክኖሎጂዎቹ ዘርፍ የተቀመጠዉ ቴክኖሎጂዉ ከሚሰጠዉ አገልግሎት አንጻር ነዉ፡፡

Science Innovation and Indigenous Technology Directory Science Innovation and Indigenous Technology Directory

Content with Technologies Manufacturing .

ፓንቺንግ ማሽን

የተለያዩ ብረታ ብረቶች፣እንጨቶችና ቆዳዎች ላይ ቅርፅ ያላቸው ቀዳዳ ማውጣት ሲሆን የተሰራውም ሙሉ ለሙሉ ከብረት ነው፡፡ አሰራሩ፡- ልክ እንደ መኪና ስፌት የሚሰፋ ሰንጀር መሰል ተደርጎ ነው፡፡ ስለሆነም በተለያዩ ቦታዎች መብሳት የሚችል ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የጫማ ቀዳዳ ለማውጣት፣ የብረት ቀዳዳ ለማውጣት ወ.ዘ.ተ...

ብረት መጠምዘዣ

የተለያዩ ድፍን ብረቶችን መጠቅለል ሲሆን አሰራሩ ሙሉ ለሙሉ ብረት በሆነ አራት ማዕዘን ወይም ጠረንጴዛ መሰል አድርጎ የተሰራ ነው፡፡ የሚሰራው በእጅ በማሽከርከር ወደ ሚፈለገው አቅጣጫ የሚጠቀልል ነው፡፡ ስለሆነም ቴክኖሎጂው የሚጠይቀው ብረት ብቻ በመሆኑ በቀላሉ በመስራት በብረት ብረት ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከፍተኛ...

የአሸዋ መንፊያ

በማንዋል የሚሰራ የአሸዋ መንፊያ ሲሆን ባለው ወንፊት አማካኝነት የሚፈለገውን አሽዋ እየጣራ የሚሳልፍ ማሽን ነው፡፡

ትዊስቲንግ ማሽን (twisting machine)

ይህ መሳሪያ በሰው ጉልበት የሚሰራ ሲሆን ብረቶችን በመጠቅለል የቤት በሮችን ወይም በረንዳዎችን ለማስዋብ ይረዳል፡፡ ማሽኑ ሀገር ውስጥ በመሰራት ከዋጋ እንፃር ዝቅተኛ ሲሆን ለአጠቃቀም የሚመች መሳሪያ ነው፡፡

ኮምቼ መፍጫ ማሽን

ከትልልቅ ዲንግያ አስከ አነስተኛ ደረጃ ያሉ ዲንጋዮችንና የብሎኬት ተረፈምርቶችን በመፍጨት ለአዲስ የብሎኬት ስራ እንደግብዓት የሚቀርብ ማሽን ነው፡፡ የማሽኑ ቋት በአንዴ አስከ 25ኪሎግራም መያዝ የሚችል ሲሆን ዲንገዩንም ለመፍጨት የሚጠቀመው በውስጡ በተገጠመለት ሀመር አማካኝነት ነው፡፡ የሚሰራውም በኤሌክትሪክ...