መግለጫ

በዚህ ዳይሬክተሪ ስር የገቡ ቴክኖሎጂዎች በተቋሙ 2007 ዓ.ም ሀገር በቀል ቴክኖሎጂ የዳሰሳ ጥናት ወቅት የተሰበሰቡ ናቸው፡፡ የተሰበሰቡትም ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ከቴ/ሙያ ት/ማ/ተቋማት እና ከግለሰብ የፈጠራ ባለሙያዎች ነው፡፡ ቴክኖሎጂዎቹም ቀድሞ የነበሩ ቴክኖሎጂዎች መሰረት በማድረግ ማሻሻያ የተደረገባቸውና ከውጪ እንዲሁም ሀገር ውሰጥ ከነበሩት የተቀዱ ናቸው፡፡ ዳይሬክተሪው በአጠቃላይ ቴክኖሎጂዎቹ የሚገኙበት አድራሻ፣ ስለ ቴክኖሎጂው አጠቃላይ መረጀና የቴክኖሎጂው ዘርፍ እንዲሁም ፎቶ ይዞል፡፡ የቴክኖሎጂዎቹ ዘርፍ የተቀመጠዉ ቴክኖሎጂዉ ከሚሰጠዉ አገልግሎት አንጻር ነዉ፡፡

Science Innovation and Indigenous Technology Directory Science Innovation and Indigenous Technology Directory

Content with Technologies TVET .

ብሎኬት መደርደሪያ ማሽን

ሥራው- የተለያየ ቅርፅ የአላቸውን ብሎኬት ማምረትና በቅድም ተከተል መሠረት መደርደር ነው፡፡ የተሰራው ከብረት ሆኖ ከወለሉ ጋር ቋሚና በ90 ድግሪ በደንብ የተተከለ ነው፡፡ ያለ ምንም ጉዳት ብሎኬቶችን በስርዓት ያስቀምጣል፡፡

የማር መጭመቂያ

ስራው ማርን በመጭመቅ ፈሳሹና ደረቁን የማር ክፍል መለየት ነው፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ በማኑዋል ማለትም በእጅ በማሽከርከር የሚሰራና ሙሉ ለሙሉ ሀገር ውስጥ በሚገኙ ቁሶች የተሰራ ነው፡፡ ማር ወደ መሳሪያው ገብቶ በተዘጋጀለት መጭመቂያ ሲጨመቅ የማሩን ፋሳሹን ክፍል በማውጣት ሰፈፉንና የማር ወለላውን ይለያል፡፡

ፓንቺንግ ማሽን

የተለያዩ ብረታ ብረቶች፣እንጨቶችና ቆዳዎች ላይ ቅርፅ ያላቸው ቀዳዳ ማውጣት ሲሆን የተሰራውም ሙሉ ለሙሉ ከብረት ነው፡፡ አሰራሩ፡- ልክ እንደ መኪና ስፌት የሚሰፋ ሰንጀር መሰል ተደርጎ ነው፡፡ ስለሆነም በተለያዩ ቦታዎች መብሳት የሚችል ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የጫማ ቀዳዳ ለማውጣት፣ የብረት ቀዳዳ ለማውጣት ወ.ዘ.ተ...

ብረት መጠምዘዣ

የተለያዩ ድፍን ብረቶችን መጠቅለል ሲሆን አሰራሩ ሙሉ ለሙሉ ብረት በሆነ አራት ማዕዘን ወይም ጠረንጴዛ መሰል አድርጎ የተሰራ ነው፡፡ የሚሰራው በእጅ በማሽከርከር ወደ ሚፈለገው አቅጣጫ የሚጠቀልል ነው፡፡ ስለሆነም ቴክኖሎጂው የሚጠይቀው ብረት ብቻ በመሆኑ በቀላሉ በመስራት በብረት ብረት ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከፍተኛ...

ተጣጣፊ የእንጀራ ምጣድ፤ /Hand cutting shear

ይህ ምጣድ አሁን በሀገሪቱ በተለይም በከተማዎች ያለውን የቦታ ጥበት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የተሰራ ሲሆን በመተጣጠፍ መቀመጥ የሚችል ነው፡፡