Skip to Content

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ1

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ2

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ3

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ4

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ5

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ6

Tech Science TV Tech Science TV

TECHIN DOCUMENTARY

Latest News Latest News

ኢትዮጵያ ከIAEA ጋር የአምስት አመት ፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረመች

የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ (IAEA) ከ2018 እስከ 2023 ባሉት አምስት ተከታታይ አመታት የሚተገብር ሰፊ ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ጋር መፈራረሙ ተገለፀ፡፡ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኩል የተፈረመው ይህ የአምስት አመት ፕሮጀችት በዋናነት በግብርና፤ በጤና፤ በኢንዱስትሪ፤ በውሃ ሃብት አያያዝ እና በጨረራ መከላከል ላይ ያተኮረ ሲሆን ከ2018 እስከ 2023 ለ5 አመታት ትግባራዊ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡

ዋና መቀመጫውን በቬና ኦስትሪያ ያደረገው አለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ (IAEA) በዚህ የአምስት አመት ፕሮጀክት ላይ ለኢትዮጵያ የፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ የተስማማ ሲሆን ይህም በኒውክሌር ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ያለውን የሰው ሃይል እጥረት እንደሚቀርፍ ታምኖበታል፡፡

ስምምነቱን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሹመቴ ግዛው እና የአለም አቀፉ የአቶሚክ ሃይል ኤጀንሲ የቴክኒካል ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ዳዙ ያንግ የተፈራረሙ ሲሆን በአጠቃላይ በስምምነቱ ኢትዮጵያ በኒውክሌር ቴክኖሎጂ የምታደርገውን ጅምር እንቅስቃሴ አንደሚያግዝ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

ምንጭ፡ IAEA


// ]]>