ድሮኖች (ሰዉ አልባ በራሪዎች) ለግብርና

ድሮኖች ወይም ሰዉ አልባ በራሪዎች ከዚህ በፊት በስፋት ጥቅም ላይ ይዉሉ  የነበሩት ወታደራዊ ቅኝቶችን እና ጥቃቶችን ለማድረስ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን እነዚህን የቅኝት እና የዉትድረና በራሪዎችን ለግብርና ስራ ቅኝት እና ቁጥጥር ስራ መዋል ጀምረዋል፡፡  በድሮኖች የሚደረገዉ ቅኝት ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ ይዉል የነበረዉን ከሳተላይት በሚገኝ  ምስል ላይ በመመስረት የሚደረገዉን የቅኝት ስራ ያስቀረ እና ይታዩ የነበሩ ጉድለቶችን የቀረፈ ቴክኖሎጂ ነዉ፡፡ በሰዉ አልባ ድሮኖች በሰፋፊ የእርሻ መሬቶች ላይ የሚደረግ ቅኝት ከመስኖ እና ዉሃ አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ጨምሮ የአፈር ልዩነት እና የመሳሰሉትን ሁኔታዎች ሰዉ በያዙ ሂሊኮፍተሮች ይደረግ ከነበረዉ ቅኝት ባነሰ ወጪ እና ጊዜ  ሰፋ ያለ መረጃ መሰብሰብ እና ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡

የግብርና ቅኝት ድሮኖቹ በጂፒኤስ፣ ዲጂታል ራዲዮ እንዲሁም አነስ ያሉ የሴንሰር ቴክኖሎጂ  የተዋቀሩ  ናቸዉ፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ ገበሬዎች ለሰፋፊ የእርሻ ልማት ቅኝት ያዉሉት የነበረዉን የሰዉ ጉልበት፣የገንዘብ እና ይባክን ነበረዉንም ሰአት ከማስቀረቱም በተጨማሪ ገበሬዎች የተሻለ ምርት እነዲሰበስቡ ይረዳል፡፡ የዚህን ቴክኖሎጂ ጽንሰ ሃሳቦች በመዉሰድ የሀገራችንን መልከአ ምድር እና የአየር ንብረት ባገናዘበ መልኩ መተግበር ከተቻለ በአሁኑ ሰአት በዉጭ እና የሀገር ዉሰጥ ባለሀብቶች በሀገሪትዋ የተለያዩ ክልሎች የተጀመሩ ሰፋፊ የእርሻ ኢነቨስትመንቶች እንዲሁም የመንግሰት የስኳር ፐሮጀክቶች ላይ ከፍተኛ ዉጤት የሚያስገኝ እና በሀገሪቷ የግብርና ዘርፍ ሽግግር ላይ ከፍተኛ አስተወጽኦ ማበርከት የሚችል ቴክኖሎጂ ነዉ፡፡