አዩዲ ከካረቦን ዳይ አክሳይድ እና ውሃ የሚመረት ነዳጅ አገኘ፡፡

በፈረንጆች  2015  ከታዩት አዳዲስ የቴክኖሎጂ  ግኝቶች መካከል አዩዲ( Audi ) የተባለው የጀርመን የመኪና አምራች ኩባንያ  ጥሩ ዜናን ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ ይህም  የመኪና ማምረቻው ከ ካረቦን ዳይ አክሳይድ እና ውሃ  የሚመረት ነዳጅ መፍጠሩ ነው፡፡ ይህም በበካይ ጋዝ ልቀት ከባቢ አየርን ከመጉዳት አንፃር  ለሚብጠለጠለው ሌላው የጀ ርመን ኩባንያ Volkswagen ታሪክ እፎይታን የሰጠ ነው፡፡አዩዲ( Audi ) ከ ካረቦን ዳይ አክሳይድ እና ውሃ  ዘይት   ነዳጅ  የሚመረትበትን ሂድት ይፋ አድርጓል፡፡ በኤሌክተሮላይሲስ ሂደት እነፋሎት ወደ ሃይደሮጂን እና ውሃ ከተቀየረ በኋላ የተገኘው ሃይደሮጂን ከተጠራቀመ ካረቦን ዳይ አክሳይድ  ጋር  በማዋሀድ   የሚፈጠረውን  ፈሳሽ  በማጣራት ወደ ነዳጅነት መቀየር ይቻላል፡፡ ሂደቱ ገና በቤተ-ሙከራ ያለ ቢሆንም ላዲስ የነዳጅ ምንጭ  እነደሚሆን ተሰፋ ተጥሎበታል፡፡