Version 1.0
Last Updated by rihana sani
2/26/18 9:09 AM
Status: Approved
አሁን ባለንበት ዘመን ላይ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለሰው ልጆች የትኛውም ችግር መፍትሄ ስለመሆኑ በርካታ ጥናቶችንና ማሳያዎችን ማቅረብ ብዙም ከባድ አይደለም፡፡ እዚህም እዚያም ውጤቱና ፋይዳው አይናችን ስር ነው፡፡ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ለማንኛውም ጉዳይ፣ በማንኛውም ቦታ፣ ሁልጊዜም፣… መጠቀማችንና እሱኑ የመፍትሄ አካል አድርገን መውሰድ ከጀመርን ከራረመ፡፡ ዓለም ላይ ግብርናው፣ ትምህርቱ፣ የለት- ተለት ህይወታችን፣ ማህበራዊ ኑሮው፣ ኢኮኖሚው፣ ወዘተ የላቀ እመርታ ለማሳየት ብሎም ለውጥ ለማምጣት የሳይንስና ቴክኖሎጂ እገዛ የግድ ያሻዋል፡፡ ይህም በምርጫ የምናደርገው ብቻ ሳይሆን ለውጥን የፈለገ ሁሉ የግድ ሊከተለው እንደሚገባ በርካታ አስረጂዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
Download (2.7MB) Get URL or WebDAV URL.