Back
stic_techsciencebookparttwo
stic_techsciencebookparttwo

Version 1.0
ከሰው ልጅ ህይወት ጋር በጥብቅ ከተቆራኙና የህልውና መሰረት ከሆኑ መስኮች ውስጥ ግብርና ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ ይህ ዘርፍ ከ10ሺህ ዓመታት በላይ እንዳስቆጠረም የተለያዩ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ዘርፍ ከጊዜው እና ከሰው ልጆች እድገት ጋር በሁሉም ቦታ ላይ እኩል ጎልብቷል (አቅሙን አዳብሯል) ማለት አይቻልም፡፡ በብዙዎቹ ታዳጊ ሀገራት ውስጥ በአዝጋሚ የለውጥ ጎዳና ውስጥ በመጓዝ ላይ ነው፡፡ ኋላ ቀር የሚባሉ የግብርና ተግባራት ለእድገቱ አዝጋሚነት ዋነኛ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች መምጣት ጋር ተያይዞ ለዘመናት የግብርናው ሳይንስ ትኩረት አድርጎ የቆየው የምርት መጠንን በማሳደግ ላይ ነበር፡፡… በዚህ አሰራር ምርቶች በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ ቢያሳዩም በታዳጊ ሀገራት ያሉ ድሆችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ግን በአግባቡ አልተቀረፉም፡፡
