ቅጅ መብት ምንድን ነው?

የቅጅ መብት ማለት አንድን የአዕምሮ ውጤት የሆነን የሥነ ጽሑፍ፣ የኪነጥበብ፣ የሥነ-ጥበብ፣ የዕደ-ጥበብ፣ የኮምፒዩተር ኘሮግራም ወይም የፎቶግራፍ ሥራ ለሠራ ግለሰብ/ግለሰቦች የሚሰጥ መብት ሲሆን የተዛማጅ መብት ማለት ደግሞ ከላይ የተጠቀሱትን የቅጅ መብት የሚያስገኙ የፈጠራ ሥራዎችን ተንተርሰው በሥራው ላይ የሚሳተፉ ከዋኞች፣ የድምፅ ሪከርዲንግ ኘሮዲውሰሮች እና የብሮድካስቲንግ ድርጅቶች የሚያገኙት መብት ነው፡፡ ማንኛውም የሥራ አመንጪ የሥራው ዓላማና የጥራት ደረጃ ግምት ውስጥ ሳይገባ ሥራው ወጥ (ኦርጅናል) ከሆነ እና ግዙፍነት ካገኘ ወይም ከተቀረፀ ሥራውን በማውጣቱ ብቻ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጥበቃ ያገኛል፡፡ የፈጠራ ሥራውን የሰራ ግለሰብ ሥራውን የማባዛት፣ የመተርጎም፣ የማመሳሰል፣ የማቀናበር ወይም ወደ ሌላ አይነት የመቀየር፣በሽያጭ ወይም በኪራይ ኦሪጅናል ሥራውን ወይም ቅጅውን የማከፋፈል፣ ኦሪጅናል ሥራን ወይም ቅጅውን ለህዝብ የማሳየት መብት ይኖረዋል፡፡y..

ንግድ ምልክት ምንድን ነው?

ንግድ ምልክት ማለት የአንድን ሰው ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ከሌሎች ሰዎች ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ለመለየት የሚያስችል የሚታይ ምስል ነው፡፡ ምልክቱም ቃላቶችን፣ ንድፎችን፣ ዲዛይኖችን፣ ፊደሎችን፣ ቁጥሮችን፣ ቀለሞችን ወይም የእነዚህን ቅንጅት ሊይዝ ይችላል፡፡ የንግድ ምልክት ጥበቃ ማድረግ የአምራቹን ወይም የነጋዴውን መልካም ስምና ዝና ለመጠበቅ፣ በዕቃዎችና አገልግሎቶች መካከል መሳከርን ለማስወገድ፣ ነጻ ገበያን ለማበረታታት፣ የሸማቹን ጥቅም ለመጠበቅ፣ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲዳብር ለማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡

ፓተንት ምንድን ነው?

ፓተንት ማለት ለአንድ አዲስ የፈጠራ ስራ ወይም ከዚህ በፊት በነበረ ፈጠራ ላይ ለተሰራ አዲስ የማሻሻያ የፈጠራ ስራ የሚሰጥ መብት ሲሆን መብቱ ለተወሰነ ጊዜ የሚያገለግልና ለባለፓተንቱ ብቸኛ መብት የሚያጎናጽፍ ህጋዊ የጥበቃ መብት ነው፡፡ ባለፓተንቱ ፓተንት ያገኘበትን የፈጠራ ስራ ለማከራየት፤ ለመሸጥ ፤ በዉርስ ለማስተላለፍ፤ በሱ ለመገልገል ወይም በሌላ በማናቸዉም መንገድ ለመጠቀም ህጋዊ መብት የሚኖረው ሲሆን ለፈጠራው የተሰጠዉ የጥበቃ ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ ሶስተኛ ወገኖች ከባለፓተንቱ ፈቃድ ካላገኙ በስተቀር ፓተንት የተሰጠበትን ፈጠራ መጠቀም አይችሉም፡፡

Recent posts
ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ
25 May 2022

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአእምሯዊ ንብረት ምንነት፣ በሕግ ማዕቀፎችና በምዝገባ ስርዓት ዙሪያ ለክልልሎችና ከተማ መስተዳድሮች...

Read More
የከተማ መስተዳድሮችና የክልሎች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃና ልማት ለማጠናከር ሚናቸው የጎላ እንደሆነ ተጠቆመ
24 May 2022

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከከተማ መስተዳድሮችና ከክልሎች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮዎችና ኤጀንሲዎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች በአእምሯዊ ንብረት...

Read More
የዓለም አእምሯዊ ንብረት ቀን #WorldIPDay  በሀገራችን በተለያዩ ሁነነቶች በድምቀት ተከብሯል።
29 Apr 2022

የዓለም አእምሯዊ ንብረት ቀን #WorldIPDay  በሀገራችን ሚያዝያ 20-21/2014ዓ.ም በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ግቢ ውስጥ በድምቀት ተከብሯል። የዘንድሮው የዓለም አእምሯዊ ንብረት ቀን...

Read More
በፈጠራ ስራዎች ውድድር አሸናፊዎች ሽልማት ተሰጠ
29 Apr 2022

በፈጠራ ስራዎች ውድድር አሸናፊዎች ሽልማት ተሰጠ የዓለም አእምሯዊ ንብረት ቀንን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው አውደ ርዕይ ላይ የፈጠራ ስራዎች ውድድር በማካሄድ...

Read More
ፓናል ውይይት ተካሄደ
28 Apr 2022

ፓናል ውይይት ተካሄደ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እና ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር ባከበረው የዓለም አእምሯዊ...

Read More
World IP DAY Exhibition
20 Apr 2022

IP and Youth: Innovating for a Better Future The Ethiopian Intellectual Property Authority will be celebrating this year’s World IP...

Read More
Contact Info

Email : info@eipo.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
FAX :-  +251 115 52 92 99
25322/1000

Usefull Links
Location