ሀገራዊ ዕድገትን ለማፋጠን አእምሯዊ ንብረትን በልማት መሳሪያነት መጠቀም እንደሚገባ ተጠቆመ

==============================

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከአለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ረቂቅ የአእምሯዊ ንብረት ፖሊሲና ስትራቴጂ ማጸደቅና ተግባራዊ ማድረግ ሀገራዊ ዕድገትና ልማትን ለማፋጠን አበርክቶው የጎላ እንደሆነ የተለያዩ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሰኔ 09/2014 ዓ.ም ባስተቸበት ወቅት ተጠቆመ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አእምሯዊ ንብረት ዘርፍን በልማት መሳሪያነት በመጠቀም የሀገሪቷን ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገትን ለማፋጠን መንግስት እየሰራ እንደሚገኝ በመክፈቻ ንግግራቸው ተናግረዋል፡፡ የአእምሯዊ ንብረት ውጤቶችን በአግባቡ ለማስተዳደር፣ ለማመንጨት፣ ለገበያ በማዋልና ለማልማት ከፍተኛ አበርክቶ የሚኖረውን የአእምሯዊ ንብረት ረቂቅ ፖሊሲና ስትራቴጂ በማጸደቅና ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ አክለው ገልጸዋል፡፡

ሀገራችን በ2030 በአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የተለመችውን ራዕይ ለማሳካት የብሄራዊና የየዘርፎች ፖሊሲዎችንና ዕቅዶችን ውጤታማ ለማድረግ ፖሊሲው ትርጉም ባለው አግባብ እንዲደግፍ ራዕይ የሰነቀ እንደሆነ በቀረበው ሰነድ ላይ ተጠቁሟል፡፡

ረቂቅ ፖሊሲውና ስትራቴጂው 13 የትኩረት መስኮችን የለየና በርከት ያሉ የትግበራ ስልቶችን በማካተት የተዘጋጀ እንደሆነ የዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት አማካሪ ጌታቸው መንግስቴ ባቀረቡት ሰነድ ላይ ተናግረዋል፡፡ አዳዲስና በስራ ላይ ያሉ የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት፣ አእምሯዊ ንብረትን በተለዩ ሀገራዊና የየዘርፍ ፖሊሲዎች ላይ ማካተት፣ ጠንካራ የአእምሯዊ ንብረት አስተዳደርና ጥበቃ ስርዓት መዘርጋት፣ ተመራማሪዎችና የፈጠራ ሰራተኞች የአእምሯዊ ንብረት ውጤቶችን እንዲያመነጩ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣ ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎችን ወደ ገበያ በማውጣት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ፣ የውጪ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ጥቅም ላይ የሚውሉበትን አሰራር መፍጠር፣ የአእምሯዊ ንብረት የህግ ተፈጻሚነትን ማጠናከር፣ የዘርፉን ግንዛቤ በህዙቡ ዘንድ ማስረጽ ፖሊሲው ከለያቸው የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል በዋናነት እንደሚጠቀሱ በቀረበው ሰነድ ላይ ተመላክቷል፡፡

ፖሊሲው ለ10 ዓመት የአእምሯዊ ንብረት ዘርፉን እንዲመራ የተቀረጸ ሲሆን በየአምስት ዓመቱ የአተገባበር ግምገማ በማከናወን ያመጣውን ለውጥ በመገምገም ወቅቱን የዋጀ ማሻሻያ በማድረግ እንደሚተገበር ተገልጿል፡፡ ፖሊሲው በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር መሪነትና የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አባል የሚሆኑበት ብሄራዊ የአእምሯዊ ንብረት ምክር ቤት በማቋቋም እንደሚተገበር በሰነዱ ላይ ተመላክቷል፡፡

ከተለያዩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተገኙ ከፍተኛ አመራሮች የቀረበውን ረቂቅ ፖሊሲና ስትራቴጂ መነሻ በማድረግ ለፖሊሲው ማጠናከሪያ ገንቢ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡

+2

Share on facebook
Facebook
Share on twitter
Twitter
Share on linkedin
LinkedIn
Contact Info

Email : info@eipo.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
FAX :-  +251 115 52 92 99
25322/1000

Sitemap
Usefull Links