የቅጅ መብት ማለት አንድን የአዕምሮ ውጤት የሆነን የሥነ ጽሑፍ፣ የኪነጥበብ፣ የሥነ-ጥበብ፣ የዕደ-ጥበብ፣ የኮምፒዩተር ኘሮግራም ወይም የፎቶግራፍ ሥራ ለሠራ ግለሰብ/ግለሰቦች የሚሰጥ መብት ሲሆን የተዛማጅ መብት ማለት ደግሞ ከላይ የተጠቀሱትን የቅጅ መብት የሚያስገኙ የፈጠራ ሥራዎችን ተንተርሰው በሥራው ላይ የሚሳተፉ ከዋኞች፣ የድምፅ ሪከርዲንግ ኘሮዲውሰሮች እና የብሮድካስቲንግ ድርጅቶች የሚያገኙት መብት ነው፡፡ ማንኛውም የሥራ አመንጪ የሥራው ዓላማና የጥራት ደረጃ ግምት ውስጥ ሳይገባ ሥራው ወጥ (ኦርጅናል) ከሆነ እና ግዙፍነት ካገኘ ወይም ከተቀረፀ ሥራውን በማውጣቱ ብቻ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጥበቃ ያገኛል፡፡ የፈጠራ ሥራውን የሰራ ግለሰብ ሥራውን የማባዛት፣ የመተርጎም፣ የማመሳሰል፣ የማቀናበር ወይም ወደ ሌላ አይነት የመቀየር፣በሽያጭ ወይም በኪራይ ኦሪጅናል ሥራውን ወይም ቅጅውን የማከፋፈል፣ ኦሪጅናል ሥራን ወይም ቅጅውን ለህዝብ የማሳየት መብት ይኖረዋል፡፡y..
ንግድ ምልክት ማለት የአንድን ሰው ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ከሌሎች ሰዎች ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ለመለየት የሚያስችል የሚታይ ምስል ነው፡፡ ምልክቱም ቃላቶችን፣ ንድፎችን፣ ዲዛይኖችን፣ ፊደሎችን፣ ቁጥሮችን፣ ቀለሞችን ወይም የእነዚህን ቅንጅት ሊይዝ ይችላል፡፡ የንግድ ምልክት ጥበቃ ማድረግ የአምራቹን ወይም የነጋዴውን መልካም ስምና ዝና ለመጠበቅ፣ በዕቃዎችና አገልግሎቶች መካከል መሳከርን ለማስወገድ፣ ነጻ ገበያን ለማበረታታት፣ የሸማቹን ጥቅም ለመጠበቅ፣ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲዳብር ለማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡
ፓተንት ማለት ለአንድ አዲስ የፈጠራ ስራ ወይም ከዚህ በፊት በነበረ ፈጠራ ላይ ለተሰራ አዲስ የማሻሻያ የፈጠራ ስራ የሚሰጥ መብት ሲሆን መብቱ ለተወሰነ ጊዜ የሚያገለግልና ለባለፓተንቱ ብቸኛ መብት የሚያጎናጽፍ ህጋዊ የጥበቃ መብት ነው፡፡ ባለፓተንቱ ፓተንት ያገኘበትን የፈጠራ ስራ ለማከራየት፤ ለመሸጥ ፤ በዉርስ ለማስተላለፍ፤ በሱ ለመገልገል ወይም በሌላ በማናቸዉም መንገድ ለመጠቀም ህጋዊ መብት የሚኖረው ሲሆን ለፈጠራው የተሰጠዉ የጥበቃ ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ ሶስተኛ ወገኖች ከባለፓተንቱ ፈቃድ ካላገኙ በስተቀር ፓተንት የተሰጠበትን ፈጠራ መጠቀም አይችሉም፡፡
የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን #EIPA ከዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት #WIPO ባገኘው ድጋፍ የአእምሯዊ ንብረት ግንዛቤን ለማሳደግ የላቀ ድርሻ የሚኖረውን የአእምሯዊ...
Read Moreበባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ ፋይን አርትስና ዲዛይን ኮሌጅ የፊልም ፕሮዳክሽን ትምህርት ክፍል እና በመልቲቾይስ /ዲኤስቲቪ ኢትዮጵያ የጋራ...
Read More============================== ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከአለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ረቂቅ የአእምሯዊ ንብረት ፖሊሲና ስትራቴጂ ማጸደቅና ተግባራዊ ማድረግ ሀገራዊ...
Read Moreየባለስልጣኑ የ2014 ዕቅድ አፈጻጸም የተሻለ እንደሆነ ተጠቆመ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2014 በጀት ዓመት በዝግጅት፤ በቁልፍ ተግባራት እና በአበይት ተግባራት ዋና...
Read Moreየኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአእምሯዊ ንብረት ምንነት፣ በሕግ ማዕቀፎችና በምዝገባ ስርዓት ዙሪያ ለክልልሎችና ከተማ መስተዳድሮች...
Read Moreየኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከከተማ መስተዳድሮችና ከክልሎች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮዎችና ኤጀንሲዎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች በአእምሯዊ ንብረት...
Read More